Winning entries could not be determined in this language pair.There were 5 entries submitted in this pair during the submission phase. Not enough votes were submitted by peers for a winning entry to be determined.Competition in this pair is now closed. |
የ«ላ ቶማቲና» አቢዮትን ያስጀመረችውን ያችን የመጀመሪያ ወሳኝ ቲማቲም የወረወራት ማን ነበር? እውነቱን ለመናገር ይህን ማንም አያውቅም። ምናልባትም ፀረ-ፍራንኮ አመፅ ወይም ከቁጥጥር ውጭ የወጣ የበዓል አከባበር ሊሆን ይችላል። በጣም ተቀባይነት ያለው ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ በ1945ቱ የሎስ ጃይጋንተስ (በውሃ ከተነከረ ወረቀትና ከማጣበቂያ የሚሰራ ግዙፍ አሸንጉሊት በመያዝ በሚደረግ ጉዞ) ክብረ-በዓል ላይ፣ የአካባቢው ሰዎች ትኩረትን ለመሳብ ሲሉ ለመረበሽ እያሰቡ ነበር። በአቅራቢያቸው ከነበረ የአትክልት ጋሪ ደረሱና የበሰሉ ቲማቲሞችን መወራወር ጀመሩ። ሁኔታው ጅምላ የፍራፍሬዎች በረራ ትርምስ እስከሚመስል ድረስ ስለሁኔታው ግንዛቤ ያልነበራቸው የዳር ተመልካቾችም ተሳታፊ ሆኑ። የድርጊቱ ጀማሪዎች ለቲማቲም አቅራቢዎቹ መልሰው ለመክፈል የተገደዱ ሲሆን፣ ይህም ሆኖ ተጨማሪ የቲማቲም ድብድቦች በድጋሜ እንዳይከሰቱ ሊያስቆም — እናም የአዲሱን ልማድ መወለድ ሊያሰቀር አልቻለም። ከህግ ውጭ እንዳይስፋፋ በመፍራት፣ ባለስልጣናት በ1950ዎቹ ተከታታይ እገዳዎችን ተግባራዊ አድርገዋል፣ አገዳዎቸን አላልተዋል ከዚያም መልሰው ተግባራዊ አድርገዋል። በ1951፣ ህዝቡ ከማረሚያ ቤት እንዲለቀቁ ተቃውሞ እስካሰማበት ጊዜ ድረስ፣ ህጉን የተላለፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ማረሚያ ቤት ገብተው ነበር። በቲማቲም እገዳዎች ላይ የተደረገው የታወቀው አምቢተኝነት የተከናወነው፣ በ1957 የእገዳው ተቃዋሚዎች የአስከሬን ሳጥንና የሰልፍ ጉዞን ያካተተ የቲማቲም አምሳያ ቀብር በአከናወኑበት ወቅት ነው። ከ1957 በኋላ፣ የአካባቢው አስተዳደር ከሁኔታው ጋር ተስማምቶ ለመቀጠል በመወሰን የተወሰኑ ህጎችን አስቀምጦ አስገራሚውን ልማድ ተቀበለ። ምንም እንኳ ቲማቲም ዋናውን ቦታ ቢይዝም፣ የአንድ ሳምንት የባዕል አከባበሮች ወደ መጨረሻው የጨዋታ ውድድር መዳረሻ ይሆናሉ። በጎዳና ላይ ጉዞ፣ በሙዚቃና በርችት የቡኖይል ጠባቂ ቅዱሳን፣ ድንግል ማርያም እና ቅዱስ ልዊስ ቤርትራንድ በአስደሳቹ የስፔን ፋሽን የሚከበሩበት በዓል ነው። ለመጪው ግጥሚያ ጥንካሬ ለማሰባሰብ፣ በፍልሚያው ዋዜማ «ኢፒክ ፔላ» የተባለ ከሩዝ፣ ከባህር ምግብ፣ ከሳፍሮንና ከወይራ ዘይት የተሰራ የቫሌንሽያ መገለጫ የሆነ ታዋቂ ምግብ ይቀርባል። ዛሬ ዛሬ፣ ይህ ስርዓት-አልባ ክብረ-በዓል የተወሰነ ቅደም ተከተል አለው። አዘጋጆቹ ለምግብነት የማይውሉ ልዩ የቲማቲም ዝርያዎችን ለአመታዊ ሁነቱ ሲሉ ብቻ እስከማምረት ደርሰዋል። ክብረ-በዓሉ የሚጀምረው ከጥዋቱ 4 ሰዓት አካባቢ ተሳታፊዎች በሚያሙለጨልጭ ፖል ላይ የተቀመጠን የአሳማ ስጋ ለመውሰድ በሚያደርጉት ውድድር ነው። ተመልካቾች በጎዳናዎች እየዘመሩና እየደነሱ ማቀላቀያዎችን ውሃ በቱቦ ይጨምሩባቸዋል። እኩለ ቀን ላይ የቤተ-ክርስቲያኑ ደወል ሲመታ፣ ቲማቲም ተጭነው የቆሙት የጭነት መኪናዎች በከተማው ውስጥ ይሽኸረኸራሉ፣ «ቶ-ማ-ቴ፣ ቶ-ማ-ቴ» የሚል ህብረት ዝማሬ ከፍ ብሎ ይሰማል። ከዚያም፣ የውሃ መድፍ በሚተኮስበት ጊዜ፣ ዋናው ሁነት ይጀመራል። ይህም በሁሉም አቅጣጫ ተሳታፊዎችን ለማጥቃት ቲማቲሞችን ደፍጥጦ ለመወርወር አረንጓዴ መብራት ነው። የእረጅም ርቀት ቲማቲም ውርወራዎች፣ ቀጥታ ቅርብ ገዳዮች፣ መካከለኛ ርቀት ጠምዛዛ ተኩሶች። የእርስዎ ስልት ምንም ይሁን ምን፣ በሚያበቃበት ጊዜ፣ የተለየ መልክ (እና ስሜት) ይኖርወታል። ለአንድ ሰዓት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ፣ በቲማቲም የተነከሩ ቦምበኞች ቲማቲም የሚመስል ትንሽ ነገር በቀረበት የሚያዳልጥ የጎዳና ላይ ስልስ ይጫወታሉ። ሁለተኛው የመድፍ ተኩስ የፍልሚያውን መጠናቀቅ ያመለክታል። | Entry #16289 — Discuss 0 — Variant: Not specified
|
የቶማቲናን አብዮት የጀመረችውን የመጀምሪያዪቱን መከረኛ ቲማቲም የወረወረው ማን ይሆን? ይህንን ማንም አያውቅም። ምንአልባት የፀረ-ፍራንኮ አመጽ ወይም ደግሞ እንደ ቀልድ ተጀምሮ አቅሉን ያጣ አስረሽ ምችው ይሆናል ያስጀመረው። በስፋት እንደሚነገረው አፈታሪክ ከሆነ ግን፣ በ 1945ቱ የሎስ ጂያንቴ ክብረበዓል ( ትልቅ የወረቀት አሻንጉሊት የተካተተበት ትርዒት ) ነዋሪዎቹ ነውጥ በመፍጠር ትኩረት ለመሳብ ምክንያት ይፈልጉ ነበር። ይህን እያሰቡ ሳለ በአቅራቢያቸው ካለ አትክልት የጫነ ጋሪ ጋር ተገጣጠሙ፤ እናም የበሰለ ቲማቲም ከጋሪው ላይ እያነሱ መወርወር ጀመሩ። ሁኔታው የለየለት የጦር ሜዳ እስኪመስል ድረስ ቆሞ ተመልካች የነበሩት ሁሉ ቲማቲም እያነሱ ይወረውሩ ገቡ። የዚህ ድርጊት ጠንሳሾች ለቲማቲሙ ነጋዴዎቹ ካሳ እንዲከፍሉ የሚደረጉ ቢሆንም፣ የቲማቲሙን ድብድብ ደግሞ መምጣት ግን አላስቀረውም- ይህም የአዲሱ ባህላዊ ክብረበዓል ልደት ሆነ። በ1950ዎቹ የሃገሪቱ ባለሥልጣናት ከህግና ደንብ ያፈነገጠ ስርዓት አልበኝነት እንዳይነግስ በመስጋት ተከታታይ ክልከላዎችን እና መመሪያዎችን ሲያነሱና ሲጥሉ ከረሙ። በ1951 ይህንን ደንብ ችላ ያሉ ነዋሪዎች በኋላ በህዝብ አቤቱታ እስኪፈቱ ድረስ በእስር ቤት ቆይተዋል። እጅግ የሚታወሰው ተቃውሞ የተከሰተው በ1957 ነበር፤ በዚህ ጊዜ የቲማቲም ውርወራው አፍቃሪዎች የሬሳ ሳጥን የተዘጋጀለትና ሥርዓቱን የጠበቀ በቲማቲም ምስል የተሰራ ቅርፅ አበጅተው የቀብር ስነስርዓት አዘጋጁ። ከ1057 በኋላ፣ የአካባቢው መንግስት ራሱን ከሁኔታው ጋር ማስማማትን መረጠ፤ የተወሰኑ ደንቦችን በማስቀመጥም አስገራሚውን ክብረበዓል ተቀበለ። ምንም እንኳ ቲማቲም ማዕከላዊውን ቦታ ቢይዝም፣ ለሳምንት የሚቀጥለው ፈንጠዝያ በስተመጨረሻ ወደ ፍጻሜ ፍጥጫ ያመራል። ይህ የቡኖል አቃቤ የሆኑት ቅዱሳን፣ የድንግል ማርያምና የቅዱስ ሉዊስ በርትራንድ ክብረ በዓል ፣ በመንገድ ላይ ትዕይንት፣ ሙዚቃ እና በእስፓኝ ልማድ የሚሄዱ ማራኪ ርችቶች ታጅቦ የሚከበር በዓል ነው። ቀጥሎ ለሚመጣው ፍልሚያ ጉልበት ለመሰብሰብ እንዲረዳ፣ ዕውቁ የቫለንሺያ የሩዝ ምግብ ፓሊያ በባህር ምግብ፣ ሳፍሮን አበባ እና የወይራ ዘይት ተዘጋጅቶ በዋዜማው ይቀርባል። ዛሬ ዛሬ ይህ ቅጥ አልባ ክብረበዓል የተወሰነ ስነሥርዓት ተበጅቶለታል። አዘጋጆቹ ለበዓሉ ስኬት ከመጨነቃቸው የተነሳ፣ ለክብረ-በዓሉ ብቻ የሚዉሉ ለምግብነት የማይሆኑ የቲማቲም ዘሮችን እስከ ማብቀል ደርሰዋል። ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት አካባቢ ተሳታፊዎቹ በቅባታማ ዋልታ ጫፍ ላይ የተቀመጠን ሥጋ ለመያዝ ሲሻሙ ዝግጅቱ ይጀምራል። ቆሞ ተመልካቾች ዳካሪዎቹ ላይ ውሃ በመርጨት በመንገዱ ላይ ዜማ እያዜሙ ይደንሳሉ። የቤተክርስቲያኑ ደወል ቀትር መሆኑን ሲያበስር በቲማቲም የተሞሉ የጭነት መኪናዎች ወደ መሃል ከተማ ይገባሉ፤ በዚህም ጊዜ “ቶ-ማ-ቴ፣ ቶ-ማ-ቴ” የሚል ድምጽ ማስተጋባት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ የውሃ መድፍ ሲተኮስ ትርዒቱ ይጀምራል። ይህ በእሩምታና ውርወራ በሌሎች ተሳታፊዎች ላይ የቲማቲም ጥቃት እንዲከፈት የሚያበስረው ነው። የረጅም ርቀት ቲማቲም ወርዋሪዎች፣ የማያቅማሙ አጥቂዎች እና መካከለኛ ወርዋሪዎች [በየፊናቸው መወራወር ይጀምራሉ]። የርስዎ ስልት ምንም ሆነ ምን ጊዜው ሲያበቃ ሁለመናዎ እንዲሁም ስሜትዎ ፍፁም ልዩ ይሆናል። ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላ በቲማቲም የተነከሩ ወርዋሪዎች በቲማቲም ጎርፍ የተጥለቀለቀው መንገድ ላይ ሳልሳ ሲጫወቱ ሲታይ ቲማቲም መሆኑን ለማመን ይቸግራል። የሚቀጥለው መድፍ ሲተኮስ የፍልሚያው ፍጻሜ ይሆናል። | Entry #18760 — Discuss 0 — Variant: Not specified
|
በላ ቶማቲና አብዮቱ ላይ የመጀመሪያዋን እጣ ፈንታውን የወሰነው ቲማቲም የወረወረው ማነው? እውነቱን ለመናገር ማንም አያውቀውም። ምናልባት የፀረ-ፍራንኮ አመጽ ሆኖ የነበረ ሊሆን ይችላል፣ ወይም አንድ ከቁጥጥር ውጪ የወጣ ካርኒቫልም ሊሆን ይችላል። በጣም በሚታወቀው ታሪክ መሠረት ከሆነ እ.ኤ.አ. በ1945 ዓ.ም. ላይ የነበረው የሎስ ሂጋንቴስ ፌስቲቫል (አንድ ግዙፍ የወረቀት ስራ ሰልፍ) ላይ የአካባቢው ነዋሪዎች ትኩረት ለማግኘት ሲሉ ሁከት ለመፍጠር እየተዘጋጁ ነበር። በአቅራቢያቸው አንድ የአትክልት ጋሪ አገኙና የበሰሉ ቲማቲሞችን መወርወር ጀመሩ። ትዕይንቱ ወደ አንድ በጣም ግዙፍ የአትክልት ውርወራ ረብሻ እስኪያድግ ድረስ ምንም እጃቸው ያልነበረት ተመልካቾች አብረው መሳተፍ ጀመሩ። ነገሩን ያስጀመሩት ሰዎች የቲማቲም ሻጮቹን መክፈል ነበረባቸው፣ ነገር ግን ይሄ ተጨማሪ የቲማቲም ጸቦችን ከመፍጠር—እና የአዲስ ባህል ከመወለድ—አላገደውም። ባለስልጣናቱም ከህግ አገዛዝ ውጪ የሆነ ረብሻ እንዳይፈጠር በመስጋት በ1950ቹ ላይ ተከታታይ የሆኑ እገዳዎችን አውጁ፣ አላሉ እና ዳግም ተገበሩ። እ.ኤ.አ. በ1951 ዓ.ም. ላይ ህጉን የጣሱ የአካባቢው ነዋሪዎች ሕዝብ ባሰማው ተቃውሞ እስኪፈቱ ድረስ ታስረው ነበር። በቲማቲም እገዳዎቹ ላይ የታየው እጅግ ታዋቂው ድፍረት እ.ኤ.አ. በ1957 ዓ.ም. ሲሆን በዚህ ጊዜ ደጋፊዎቹ የፌዝ የቲማቲም ቀብር ስነ-ስርዓት ከነሬሳ ሳጥኑ እና ሰልፉ አሳዩ። ከ1957 ዓ.ም. በኋላ አካባቢያዊ መንግስቱ ከሁኔታው ጋር አብሮ ለመጓዝ ወሰነና ጥቂት ደንቦችን አስቀምጦ ወጣ ያለውን ባህል ተቀበለ። ምንም እንኳ ቲማቲሞቹ ዋናው ትኩረት የሚይዙ ቢሆኑም ሳምንት የሚዘልቀው የበዓል አከባበር ወደ አንድ የመጨረሻ ፍልሚያ ያመራል። ይሄ የቡኞል ጠባቂ ጻድቃን፣ የድንግል ማርያም እና የቅዱስ ሉዊ በርትራንድ በዓል ከመንገድ ላይ ሰልፎች፣ ሙዚቃ፣ እና የሪችት ስራ ጋር በአስደሳች የስፓኒሽ ባህል የሚደረግ አከባበር ነው። ዛሬ ይህ ቁጥጥር የሌለው ፌስቲቫል በተወሰነ ደረጃ ስርዓት አለው። አዘጋጆች ለአመታዊው ክስተቱ ሲባል ብቻ ልዩ የሆኑ ለመብል የማይሆኑ ቲማቲሞችን እስከማብቀል ድረስ ሄደዋል። በዓሉ ተሳታፊዎች በአንድ የሚያሟልጭ ምስሶ ጫፍ ላይ የተቀመጠ የአሳማ ስጋ ለመያዝ በሚሽቀዳደሙበት ጥዋት 4 ሰዓት አካባቢ ይጀምራል። ተመልካቾች መንገዶቹ ላይ እየዘፈኑ እና እየደነሱ ሳሉ ተሻሚዎቹን በውሃ ይረጯቸዋል። የቤተክርስትያን ደወል 6 ሰዓት ላይ ሲደውል «ቶማቴ፣ ቶማቴ!» የሚል ዝማሬ ከፍተኛ ድምጽ ላይ እየደረሰ በቲማቲም የሞሉ የጭነት መኪናዎች ወደ ከተማው ይገባሉ። ከዚያ በውሃው መድፊያው ውሃ በመርጨት ዋናው ክስተቱ ይጀመራል። ያ በሌሎች ተሳታፊዎች ላይ በቲማቲሞች የሚደረግ ሙሉ ጥቃት የሚጀመርበት ምልክት ነው። የረጅም ርቀት ቲማቲም ውርወራዎች፣ ፊት ለፊት ወርዋሪዎች፣ እና የመካከለኛ ርቀት ማስወንጨፎች። የእርስዎ ቴክኒክ ምንም ይሁን ምን ነገርየው በሚያልቅበት ጊዜ መልክዎ (እና ስሜትዎ) የተለየ ይሆናል። ለአንድ ሰዓት ከሚጠጋ ጊዜ በኋላ በቲማቲም የበሰበሱ ወርዋሪዎች በስልስ ባህር ውስጥ ይጫወታሉ። በዚህ ጊዜ ቲማቲም የሚመስል ነገር ካለ በጣም ትንሽ ነው የሚኖረው። ሁለተኛ የውሃ ተኩስ ውጊያው ያለቀ መሆኑን ያውጃል። | Entry #15523 — Discuss 0 — Variant: Not specified
|
ሇቲማቲም አብዮት መነሻ የሆነችውን የመጀመሪያዋን እዴሇኛ ተማቲም የወረወረው ሰው ማን ነው? እውነታውን ማንም አያውቀውም፡፡ ምናሌባት የጸረ-ፍራንኮ አብዮት ወይም በዴንገት እውቅናን ያገኘ ክብረበዓሌ ነው፡፡እንዯ ታዋቂው የታሪክ ማጣቀሻ ገሇጻ ከሆነ፤በ1945 የልስ ጂአንትስ ሌዩ ክብረበዓሌ ጊዜ (ጂአንት ፔፐር ማች ፓፔት ፓሬዴ), አገሬው ትኩረትን ሇማግኘት የጎዲና ሊይ ዴብዴቡ ያስፈሌጋቸው ነበር፡፡በአቅራቢያው በሚገኘው የአትክሌት ስፍራ ሊይ በመውጣት እና የበሰለ ቲማቲሞችን በመወራወር ጀመሩ፡፡ገሇሌተኛ የነበሩ ተመሌካቾች ትዕይንቱ ወዯ ከፍተኛ የፍራፍሬ ውርወራ አቢዮት ሲዛመት እነሱም ተሳተፉ፡፡መሪዎች ሇቲማቲም ጅምሊ ነጋዳዎች መሌሰው መክፈሌ ነበረባቸው፤ነገር ግን ያ በቲማቲም ዴብዴብ የሚወጣውን ወጪ ሉያስቆመው አሌቻሇም----የአዱስ ባህሌ ውሌዯት ነው፡፡ ባሇስሌጣናቱ በ1950ዎቹ የስርዓት አሌበኝት መባባስ ፍርአት ውሳኔ እንዱወስኑ እና እንዯገና ጠንከር ያሇ እገዲ እንዱያዯርጉ አስገዯዲቸው፡፡በ1951 ህጉን የተሊሇፉ ነዋሪዎች በህዝቡ ጩኸት እስኪሇቀቁ ዴረስ በእስር ቤት ታስረው ነበር፡፡በ1957 ሇተፈጠረው የቲማቲም ዴብዴብ እገዲ በዋናነት ተጠቃሽ የሚሆነው በአዯገኛ ዴፍረት የተሞሊው እና ዯጋፊዎች በሬሳ ሳጥን እና በሰሌፍ የቲማቲም ቀብር ስነስርዓት አፈጻጸም ያዯረጉበት ቀሌዴ ነበር፡፡ከ1957 በኋሊ የሀገሪቱ መንግስት በጉሌበት ሇመቆጣጠር ወሰነ እንዱሁም በስፍራው ጥቂት ህጎችን በማኖር ሌዩ የሆነውን ባህሌ ተቀበለ፡፡ ቲማቲሞቹ ማዕከሊዊውን መዴረክ ቢቆጣጠሩትም፤ሳምንታዊ ባህሊት ወዯ ፍጻሜው ጦርነት እያመሩ ነው፡፡በጎዲና ሊይ ሰሌፍ፤ሙዚቃ እና በስፔናዊያን ፋሽን የተሰራ የዯስታ ማዴመቂያ ርችቶች የሚዯረግ የቡኖሌ ፓትረን ቅደሳን፤ዴንግሌ ማሪያም እና ቅደስ ለይስ በርትራንዴ የዯስታ ስነስርዓት ነው፡፡ሇዴብዴቡ የሚሆን ጥንካሬዎትን ሇማዲበር፤በጦርነቱ ዋዜማ የፉከራ እና ቀረርቶ ግጥሞች፤የቫላንሽያውያን ጣፋጭ የሩዝ፤የባህር ምግቦች፤እርዴ እና የወይራ ዘይት ይዘጋጃለ፡፡ ዛሬ ይህ ሌቅ የሆነ የዯስታ በዓሌ የተወሰነ ዯንብ አሇው፡፡አዘጋጆች ሇዓመታዊ ዝግጅት ሌዩ ሌዩ የሆኑ የተበሊሹ ቲማቲሞችን ሇማምረት ብዙ ጥረት ያዯርጋለ፡፡ዴግሱ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ይጀምራሌ፡፡ተሳታፊዎች የአሳማ ስጋ በሚያሟሌጭ ቅባት የተነከረ እንጨት ሊይ ያሇውን የአሳማ ስጋ ሇመውስዴ እየታገለ ፌስቲቫለ ከጠዋቱ 4 ሰዓት አከባቢ ይጀምራሌ፡፡ተመሌካቾች በጎዲና እየጨፈሩና እየዘፈኑ ተጫዋቾቹን በውኃ ያጥባለ፡፡የቤተክርስቲያን ዯውሌ ከሰዓት ሲዯወሌ፤ቲማቲም የጫኑ ትሊሌቅ መኪኖች ወዯ ከተማው ይመጣለ፤”ቲ-ማ-ቲ-ም፤ቲ-ማ-ቲ-ም የሚሇው ዘፈን በከፍተኛ ዴምጽ ያስተጋባሌ፡፡ ከዚህ በኋሊ, የውኃ መዴፍ በመተኮስ ዋናው ትእይንት ይጀምራሌ፡፡አረንጓዳ መብራቱ ተሳታፊዎች ጨዋታውን እንዱጀምሩ እና የረጅም ርቀት ቲማቲም ወርዋሪዎች፤ቀጥተኛ ኢሊማ ወርዋሪዎች እና በመካከሇኛ ርቀት ውርወራዎች የቲማቲም ጦርነቱ ማስጀመሪያ ናቸው፡፡፤በምንም አይነት መንገዴ ቢሆንም፤በዚህ ሰዓት የሚሰማዎ ስሜት በጣም የተሇየ ነው፡፡ከአንዴ ሰዓት በኋሊ፤በቲማቲም የበሰበሱ ተወራዋሪዎች የሚያመሩት ጥቂት በቀራቸው ተመሳሳይ ቲማቲም በመወራወር በባህር ዲርቻ በሳሌሳ መጫወት ነው፡፡ሁሇተኛው የቲማቲም መዴፍ ተኩስ የውጊያው መጨረሻ ይሆናሌ፡፡ | Entry #18376 — Discuss 0 — Variant: Not specified
|
በቲማቲም የመወራወርን አብዮት የጀመረው የመጀመሪያውን እድለኛ ቲማቲም የወረወረው ማን ነው? እውነታው ማንም አያውቀውም። ምናልባትም የጸረ-ፈረንሳይን አመጽ፥ ወይም ከእጅ የሚወጣ በዓልን የማክበር ሊሆን ይችላል። በብዙኃን እንደታወቀው የታሪክ ዘገባ፥ በ1945 የሎስ ጊጋንትስ ክብረ በዓል (ትልቅ የሆነ ማቼ የተባለ የወረቀት አሻንጉሊት ክብረ በዓል) ጊዜ፥ የአከባቢው ሰዎች ትኩረት ለማግኘት ሲሉ ትግል ለማካሄድ እየፈለጉ ነበር። በአጠገባቸው የፍራፍሬ ማጓጓዣ በማግኘታቸው የበሰሉትን ቲማቲም መወራወር ጀመሩ። ነገሩ ያልገባቸው የዋህ የሆኑ ተመልካቾችም ከፍተኛ የሆነ በፍራፍሬ የመወራወር ጥል እስከሚለወጥበት ድረስ ተሳትፈውበታል። ወርዋሪዎቹ ለቲማቲም ነጋዴዎች የመክፈል ግደታ ነበረባቸው፤ ነገር ግን ያ በይበልጥ በቲማቲም የመደባደቡን- እና የአዲስ ባሕል ውልደትን ድግግሞሽ አላስቀረም። የሚያስፈራው ስርዓት አልበኝነቱ መጨመር፥ ባለስልጣናቱም በ1950ዎቹ ደግፈው፥ ተዝናንተው፥ ከዚያም ጨከን ያለ ቅጣት አስተላልፈዋል። በ1951፥ ሕጉን የጣሱት ነዋሪዎች ሕዝብ እንዲለቀቁ ድምጻቸውን እስኪያሰማ ድረስ ታስረዋል። በጣም ታዋቂ የሆነው ጭካኔ የተሞላበት የቲማቲም ቅጣት በ1975 ተቃዋሚዎች በሬሳ ሳጥን ውስጥ ጨምረው የቲማቲም ቀብር ብለው ሲቀልዱ እና ሰልፍ ሲያካሄዱ ተጥሎአል። ከ1957 በኋላ፥ የአገሩ መንግሥት ድብደባውን ለመቀየር፥ በዚያ ፈንታ ትንሽ ሕጎችን በማውጣት፥ እና አስገራሚውን ባሕል ለመቀበል ወሰነ። ምንም እንኳን ቲማቲሙ ማዕከላዊውን ቦታ ቢይዝም፥ ለሳምንት የሚቆየው ክብረ በዓሉ ወደ መጨረሻው ትዕይነት ያመራል። የቡኖል የቅዱሳን አማኞች፥ የድንግል ማርያም እና የሉይስ ቤርትራንድ፥ በጎዳና ላይ ቀለማት፥ በሙዚቃ እና በመብራት ዓይነት በስፔናውያን የፈንጠዚያ የሚከበር ነው። ለሚመጣው ጥል ሰውነትን ጥንካሬ እንዲኖረው ለመገንባት፥ በግጥምያው ዋዜማ ላይ የታወቀው ፓኤላ የተባለው ምግብ፥ ከሩዝ የተሠራው የታወቀው የቫለንሺያ ባሕል ምግብ፥ የባሕር ምግቦች፥ ቅመማ ያላቸው ምግቦች እና የወይራ ዘይት ይሰጣል። ዛሬ፥ ይህን ማቆም የማይቻለውን ክብረ በዓል ሥርዓት ለማስጠበቅ ተብሎ ጥቅት ሕጎች አሉት። አዘጋጆቹም ለዚሁ ለዓመታዊው በዓል የሚሆን ለምግብነት የማይውሉ የተለዩ ቲማቲሞችን እስከማምረት ድረስ ሄደዋል። ክብረበዓሉም ተሳታፊዎቹ በዘይት ተቀብቶ የተተከለውን ረጅም ምሰሶ ለመያዝ ከሮጡ በኋላ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይጀምራል። ተመልካቾቹም በጎዳና ላይ እየዘመሩና እየደነሱ ሲሄዱ ቲማቲም በተወራወሩት ላይ ውኃ ይረጫሉ። ቀትር ላይ የቤተ ክርስቲያን ደወል ሲደወል፥ቲማ-ቲ-ሚ የሚለው መዝሙር በከፍተኛ ድምጽ ሲዘመር፥ የቲማቲም ኩንታል የተሸከሙ ገልባጭ መኪናዎች ከተማው ውስጥ ይቆማሉ። ከዚያም፥ ውኃ ከመርጨት ጋር፥ ታላቁ ክስተት ይጀምራል። ያም ቲማቲሙን ለመደፍጠጥ እና ሌሎች ተሳታፊዎችን በቲማቲሙ ለማጥቃት አረንጓደ መብራት ነው። ቲማቲሙን ረጅም ርቀት ወርዋሪዎች፥ የቅርብ ርቀት ገዳዮች፥ እና መካከለኛ ርቀት ወርዋሪዎች ይያዛሉ። ዘዴያችሁም ምንም ቢሆን፥ ጊዜው ባለቀ ጊዜ ፈጽሞ የተለየ ትመስላላችሁ (ታስባላችሁ)። ከአንድ ሰዓት በኋላ፥ የቲማቲም ደፈጣ ተኳሾች የተረፉት ጥቅት ቲማቲም መስለው የጎዳና ላይ ለስላሳ የሳልሳ ዘፈን በባሕር ውስጥ ለመጫወት ይሄዳሉ። ሁለተኛ በጠመንጃ ምልክቶች ላይ መተኮስ የጫወታው ፍጻሜ ይሆናል። | Entry #16777 — Discuss 0 — Variant: Not specified
|